Welcome

Welcome to the Ethiopian Community Association of Charlotte

We are pleased that you are visiting our new website. We hope it will serve to introduce you to the service being provided by the local Ethiopian Community association.

We also hope that you will be inspired to join us in volunteering and serving our community and contributing towards our vision: “To maintain a cohesive and cooperative Ethiopian community in the greater Charlotte-Mecklenburg area, preserving our rich Ethiopian heritage, where all members of the community are thriving and successful in their pursuits of their dreams while providing mutual support and assistance to each other”.

Please feel free to let us know your feedback anytime by pressing the “Contact Us” button at the top. We welcome all constructive thoughts, comments and suggestions!

እንኳን ደህና መጡ!

በተለያየ ገጠመኝና ሁኔታ ከሃገራችን ኢትዮጵያ ወጥተን በመላው አለም የተዘራን ኢትዮጵያውያን ቁጥር በርካታ ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል።

በሻርለትም የዛሬ 16 ዓመት ከነበረው ቁጥሩ በ10 እጅ ጨምሮ በአምስት እና ስድስጥ ሺህ መካከል እንደሚሆን የዳሰሳ ግምት አለ።

ስደት የሰው ልጅ የታሪኩ አካል ስለሆነ፤ በወጣትነት እድሜያቸው የተሰደዱና በስደት ዓለም የተወለዱትም በሚገጥማቸው የባህል አለመጣጣም ስለሚረበሹና በማንነት ጥያቄ ስለሚጠቁ፤ ወላጆች ኢትዮጵያዊ ማንነትንም ሆነ የሀገራቸውን ባህልና ታሪክ የሚያስተላልፉበትን መንገድ በማጣት ሲጨነቁና ሲያዝኑ ይስተዋላል።

ተያያዥ ችግሩ ደግሞ እርስ በርሳችን መቀራረብና መገናኘት ባለመቻላችን  ወጣት እህት-ወንድሞቻችን እንዲሁም ልጆቻችን ባልም ሚስትም ማግኘት ባለመቻላቸው ትራስ ታቅፈው እንደሚያድሩ ሲነገር እንደ ቀልድ (ፌዝ) ይታይ ይሆናል፤ ተያይዞም በዕጽ መለከፍና በአልኮል መደንዘዝም ቀጣይ ሂደቶች ሲሆኑ ጎጂነታቸው አይቀሬ ነው።

“50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፤ ለብዙ ሰው ግን ጌጥ ነው” እንዲሉ እኛም አብረን ተባብረን ብንሠራ ኢትዮጵያዊ ባህላችንን፣ ወግ-ሥርዓታችንን እና አኩሪ ታሪካችንን ለልጆቻችን በማስተላለፍልንታደጋቸው ከመቻላችን ባሻገር፤ ባለንበት ማህበረ ሰብ ውስጥ ጠቃሚና ተጠቃሚ መሆን እንደምንችል በማመን የሻርለትና አካባቢው የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማኅበርን ካቋቋምን እነሆ 16 ዓመታት አስቆጥራናል።

ኮሚዩኒቲአችን ባሳለፈው ጉዞ በርካታ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም እንደአመጣጣቸው እየመለሰ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

በተለይ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ማኅበሩ እራሱን በማጠናከር ማህበረሰቡን ሊጠቅሙ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በተለይም ለጤና፤ ለትምህርት፤ ለሥራ፣ ለመኖሪያ ቤትና  ለመጠለያ፤ ለኢሚግሬሽን እና ለመሳሰሉት ርዕሶች ትኩረትን ሰጥቶ፤ ባለሞያዎችና የሚመለከታቸውን ክፍሎች እየጋበዘ ማብራርያና እገዛ እንዲሰጡ አድርጓል፤ በማድረግም ላይ ይገኛል።

ሌላው ትልቁ የምስራችደግሞ የኮሚዩኒቲው ማኅበር ለተደራሽነትና ብቃት ያለው አገልግሎት ለማህበረሰቡ ለማስተላለፍ ያመቸው ዘንድ ይህንን ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) አዘጋጅተን ሥራ መጀመራችን ነው።

ስለዚህ በመከፋፈላችን ተጎጂዎጅ እንጂ ተጠቃሚ ባለመሆናችን በኢትዮጵያዊነት እየተገናኘን መረዳዳታችንን በማጠናከር ለልጆቻችንም ኢትዮጵያዊ እሲቶቻችንን አብረን ለማስተላለፍ እንድንበቃ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

ስለ ድረ ገጹ (ዌብ ሳይቱ) አጠቃቀም ጥያቄ ወይም አስተያየት ቢኖራችሁ የምንችለውን ያህል ለመመለስ ዝግጁዎች መሆናችንን በትህትና እየገለጽን፤ ስለመልካም ተሳትፎአችሁ በማኅበሩ ሥም ምስጋናችንን እናቀርባለን።